አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስቴር ለትግራይ ወረዳ፣ ከተማና ቀበሌ የሚሰጠውን የድጎማ በጀት የሚተላለፍበትን አሰራር አዘጋጅቶ ማጠናቀቁን ገለጸ።
የፌዴሬሽን ምክር ቤት ነሃሴ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባና በወሰነው ውሳኔ መሰረት እንዲሁም መስከረም 26 ቀን 2013 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ኢ-ህገ መንግስታዊ ምርጫን በማድረግ፣ አዲስ የክልል ምክር ቤትና ከፍተኛ የህግ አስፈጻሚ አካል በመመስረቱ ከፌደራል መንግስት ጋር ያለው ግንኙነት ከክልሉ ወረዳ ከተማና ቀበሌ መዋቅሮች ጋር እንዲሆን በፌደራል መንግስት መወሰኑ ለአሰራሩ መዘጋጀት ምክንያት ሆኗል ተብሏል።