የሀገር ውስጥ ዜና

የከተማ አስተዳደሩ በደቡብ ክልል በተለያዩ ምክንያቶች ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች 4 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ አደረገ

By Abrham Fekede

October 23, 2020

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በደቡብ ክልል በጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች 4 ሚሊየን ብር የሚገመት የገንዘብ እና የአይነት ድጋፍ አበረከተ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የገንዘብ እና 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የአይነት በጠቅላላው የ4 ሚሊየን ብር ድጋፍ ለክልሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ኃይለማርያም ተስፋዬ አስረክበዋል፡፡