የሀገር ውስጥ ዜና

የልዩ ዘመቻዎች ሀይል የኮማንዶ ትርኢት ተካሔደ

By Abrham Fekede

October 23, 2020

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ33ኛ ዙር መሰረታዊ ኮማንዶና የ10ኛ ዙር ልዩ ኃይል የፀረ ሽብር ሰልጣኞች የአየር ወለድ ትርኢት በሃዋሳ ከተማ አቀረቡ፡፡

በሄሊኮፍተር በታገዘው ትርኢት የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ምክትል ኤታማዦር ሹምና የኦፕሬሽን ዘርፍ መመሪያ ኃላፊ ጀኔራል ብርሀኑ ጁላ እና ከፍተኛ የሰራዊቱ አመራሮች የፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ ተከታትለዋል።