አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 17 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዋሽ ወንዝ ሙላት ሳቢያ በጎርፍ ተጥለቅልቆ አገልግሎት አቋርጦ የነበረው የአዋሽ 3 የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በከፊል አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡
32 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው የአዋሽ 3 የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በውሃ መጥለቅለቅ አደጋ ምክንያት ከነሐሴ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ አገልግሎት መስጠት አቁሞ ነበር፡፡