የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በኦሮሚያ ጎሮ ጉቱ ወረዳ የአንበጣ መንጋ ያደረሰውን ጉዳት ጎበኙ

By Meseret Demissu

October 29, 2020

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኦሮሚያ ጎሮ ጉቱ ወረዳ የአንበጣ መንጋ ያደረሰውን ጉዳት ጎብኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሶማሌ ክልል እና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ሲያደርጉ የነበረውን የልማት ፕሮጀክት ጉብኝቶችን በማገባደድ ነው በኦሮምያ ምስራቅ ሀረርጌ ዞን በጎሮ ጉቱ ወረዳ የአንበጣ መንጋ ያደረሰውን ጉዳት የጎበኙት።