የሀገር ውስጥ ዜና

የሰላም ሚኒስትር  ከኢትዮጵያ የሃይማኖት  ተቋማት ጉባዔ ጋር ምክክር እያካሄደ ነው

By Meseret Demissu

November 03, 2020

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)  የሰላም ሚኒስትር  ከኢትዮጵያ የሃይማኖት  ተቋማት ጉባዔ ጋር  በመተባበር  ”ሃይማኖታዊ እሴቶቻችን የአብሮነታችን እና የሰላማችን ዋስትና ናቸዉ”  በሚል መሪ ሃሳብ ምክክር እየተደረገ ይገኛል።

መድረኩን  የከፈቱት በሰላም ሚኒስቴር  የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ  አቶ ሀይላይ ብርሃኔ ÷ሁሉም ሃይማኖቶች አስተምህሯቸው ሰላምና ፍቅር በመሆኑ ለሀገሪቱ  ዘላቂ ሰላምና ዕድገት ሚናቸዉ ታላቅ ነዉ ብለዋል ።

ይህ መድረክ ኢትዮጵያ የሚያጋጥሟትን ችግሮች ለመፍታት  የሚያስችሉ  ሃሳቦችና የመፍትሄ  አቅጣጫዎች  ላይ ለመመካከር የታለመ ነው ሲሉ  ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ  ጠቅላይ ፀሐፊ  ሊቀ ትጉኃን ታጋይ ታደለ  ጉባኤዉ ባለፉት ጊዜያት ያከናወኗቸዉን ዋና ዋና ተግባራት በሪፖርት መልክ አቅርበዋል ።

“ማህበራዊ ሀብቶቻችን ከሃይማኖት አንፃር” በሚል ርዕስ የጥናት ጽሁፍ  በዶክተር ጥላሁን በጅቷል በሰላም ሚኒስቴር የባህልና ማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ቀርቦ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።

የምክክር መድረኩ  ለሁለት ቀናት  እንደሚቆይም ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።