የሀገር ውስጥ ዜና

አንቶኒዮ ጉተሬዝ የኢትዮጵያ ሰላም ለቀጠናው ወሳኝ መሆኑን ገለፁ

By Meseret Demissu

November 05, 2020

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የኢትዮጵያ መረጋጋት ለቀጠናው ወሳኝ መሆኑን ገለፁ፡፡

ዋና ፀሀፊው ድርጅታቸው በኢትዮጵያ የተጀመረው ሪፎርም ከዳር እንዲደርስና የኢትዮጵያ ህዝብ ተጠቃሚ እንዲሆን ከሁሉም ባለ ድርሻ አካላት ጋር እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

ስለሆነም የሀገሪቷ ሰላም ለምስራቅ አፍሪካ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

ድርጅታቸው ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመሆን በሀገሪቷ ሰላም እንዲወርድና ህዝቦቿም ብሩህ ተስፋ እንዲኖራቸው እንሰራለንም ነው ያሉት፡፡

በትግራይ ክልል የተፈጠረው የፀጥታ ችግር በአስቸኳይ እንዲፈታና ህዝቡ ሰላማዊ ህይወቱን እንዲቀጥል አሳስበዋል፡፡