የሀገር ውስጥ ዜና

በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ለኪነ ጥበብ ባለሙያዎችና ለአትሌቶች ገለፃ ተደረገ

By Tibebu Kebede

November 10, 2020

አዲስ አበባ፣ ህዳር 1፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ለኪነ ጥበብ ባለሙያዎች እና ለአትሌቶች በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ገለፃ ተደርጓል።

መድረኩ አሁን ሀገሪቱ ባለችበት ሁኔታ ዙሪያ የኪነ ጥበብ ባለሙያው እና አትሌቶች በትኩረት እንዲከታተሉ እና ሚዛበናዊ ግንዛቤ አንዲይዙ ለማድረግ ያለመ ነው።

በመድረኩ ላይም “በህወሓት ውስጥ የመሸገው ከሃዲ ቡድን እና ሀገራዊ አንድነታችን” በሚል ጽሁፍ ቀርቧል።

መንግስት አሁን የጀመረውን ሀግ የማስከበር ስራ ከማከናወኑ በፊት ከለውጡ ጊዜ ጀምሮ ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ያደረጋቸው ሂደቶችም ቀርበዋል።

የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች በእውቀታቸው፣ በሙያቸው እና በልምዳቸው ሀገርን ለማስቀጠል የሚደረገውን ርብርብ እንዲያግዙም ጥሪ ቀርቧል።

በአላዛር ታደለ