አዲስ አበባ ፣ ህዳር 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለመከላከያ ሠራዊት እየተደረገ ያለውን ድጋፍ ለማስተናገድ የተለያዩ የፌደራል ተቋማትን ያሳተፈ ብሔራዊ ኮሚቴ መቋቋሙን የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የሠላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሀገሪቱን ወቅታዊ ጉዳዮች አስመልክቶ በተዘጋጀ መድረክ የመከላከያ ሠራዊት እያካሄደ ያለውን ህግን የማስከበር ስራ በመደገፍ ህብረተሰቡ ፍቅርና ክብሩን እየገለጸ ይገኛል ብለዋል፡፡
በተለያየ መንገድ ለመከላከያ ሰራዊቱ እየተደረገ ያለውን ድጋፍ በአግባቡ ለማስተናገድ የተለያዩ የፌደራል ተቋማትን ያሳተፈ ብሄራዊ ኮሚቴ ተቋቁሞ ስራ መጀመሩን ሚኒስትሯ መግለጻቸውን ከሠላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።