አዲስ አበባ፣ ህዳር 3፣ 2013 (ኤፍቢሲ) ኢራን በ2015 ከኃያላን ሃገራት ጋር ከደረሰችው ስምምነት ወጭ 12 እጥፍ ዩራኒየም ማበልጸጓ ተገለጸ፡፡
ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ተቆጣጣሪ ኃይል ኤጀንሲ ኢራን 2 ሺህ 442 ኪሎግራም ያህል ዩራኒዬም ማበልጓን ነው ያፋ ያደረገው፡፡
ከአምስት ዓመታት በፊት እንድታመርት የተፈቀደላት ዩራኒየም እስከ 300 ኪሎግራም እንደነበር ይታወሳል፡፡
ኢራን አሁን ያበለጸገችው ዩራኒየም አነስተኛ ይዘት እንዳለው ነው የተገለጸው፡፡
ኢራን በፈረንጆቹ 2015 ከአሜሪካ፣ ሩሲያ፣ ብሪታንያ፣ ቻይና እና ፈረንሳይ እንዲሁም ከጀርመን ጋር በተጨማሪነት የኒውክሌር ስምምነት መድረሷ ይታወሳል፡፡
ይሁንና የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ከስምምነቱ ባለፈው አመት የወጣ ሲሆን አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት በመሆን የተመረጡት ጆ ባይደን ዳግም ወደ ስምምነቱ ለመመመለስ ፍላጎት ማሳየታቸው ተሰምቷል፡፡
ምንጭ፡-ቢቢሲ