የሀገር ውስጥ ዜና

በአዲስ አበባ ዘውዲቱ ሆስፒታል አካባቢ የእሳት አደጋ ተከስቷል

By Tibebu Kebede

November 16, 2020

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 7 ፣2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ዘውዲቱ ሆስፒታል አካባቢ የእሳት አደጋ ተከስቷል።

አደጋው ከሸራተን ወደ አምባሳደር በሚወስደው መንገድ ጫፍ ላይ በሚገኘው አደባባይ አጠገብ በሚገኝ ካፌ ላይ መነሳቱ ነው የተነገረው፡፡

የአዲስ አበባ እሳት እና አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ሰራተኞች ወደ ስፍራው አቅንተዋል።

የእሳት አደጋውን መንስኤና አጠቃላይ ዝርዝር መረጃዎችን እንደደረሰን እናቀርባለን፡፡