የሀገር ውስጥ ዜና

መንግስት ወደ ጎረቤት ሀገራት የሚሰደዱ ዜጎችን ለመቀበል ዝግጁ ነው-ጠ/ሚ ዐቢይ

By Meseret Demissu

November 17, 2020

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 8 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ መንግስት ወደ ጎረቤት ሀገራት የሚሰደዱ ወገኖችን ለመቀበል እና ወደ ቀዬአቸው ለመመለስ ዝግጁ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር  ዐቢይ አህመድ  ገለፁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስት ዐቢይ በትዊተር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷የተሰደዱ ንፁሀን ዜጎችን ንብረታቸውን ለመጠበቅ ፣ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሰብአዊ ድጋፍ ለማቅረብ እና ሲመለሱም ሰላማቸውን ለማስጠበቅ  ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።