የሀገር ውስጥ ዜና

“ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ” መርሃ ግብር በተለያዩ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችና የፌደራል ተቋማት ተካሄደ

By Tibebu Kebede

November 17, 2020

አዲስ አበባ፣ ህዳር 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) “ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ” መርሃ ግብር በተለያዩ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችና የፌደራል ተቋማት ተካሄደ።

መርሃ ግብሩ በሰላም ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚልን ጨምሮሚኒስትር ደኤታዎች እና የተቋሙ ሰራተኞች በተገኙበት ተካሂዷል።

የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል በዚሁ ወቅት፥ ክብርና አድናቆት ለሚገባው አርማችንና መከታችን ለሆነው ለመከላከያ ሰራዊታችን ክብራችሁንና ፍቅራቸውን ለገለጹ የሰላም ቤተሰቦች ከልብ ምስጋና አቅርበዋል”።

ወይዘሮ ሙፈሪሃት፥ “መከላከያችን ህዝቡን አምኖ እራሱን ሰጥቶ ጀርባውን ሳይሆን ግንባሩን ስለሀገሩና ስለህዝብ ሲል የተሰለፈ ሀይል ነውና ከክብር፣ ከምስጋና ከፍቅር ውጭ አይገባውም ነበር” ብለዋል።

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም የሚኒስቴር መስያ ቤቱ አመራሮች እና ሰራተኞች በዛሬው እለት በተካሄደው “ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ” መርሃ ግብር ላይ በመሳተፍ ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፋቸውን ገልፀዋል።

በትራንስፖርት ሚኒስቴርም “ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ” መርሃ ግብር የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስን ጨምሮ ሚኒስትር ዴኤታዎችና የተለያዩ የሥራ ክፍል ሓላፊዎች እንዲሁም አጠቃላይ ሠራተኛው በተገኙበት ተካሂዷል።

በኢፌዲሪ ባህልና ቱሪዝም ሚንስቴርም መርሃ ግብሩ የባህልና ቱሪዝም ሚንስትር ዶክተር ሂሩት ካሳውን ጨምሮ ሚንስትር ዲኤታዎች፣ አመራሮች እና ሰራኞተኞች ተካሂዷል።

የጤና ሚኒስቴር የስራ ሃላፊዎችና ሰራተኞች የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በተገኙበት፥  “ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ” በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው መርሃግብር ለጀግናው የመከላከያ ሰራዊት ያላቸውን ክብርና ድጋፍ ገልጸዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞችም “ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ” በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው መርሃ ግብር ላይ የተካፈሉ ሲሆን፥ “ለመስዋዕትነታቸሁ ክብር ሰጥተናል፣ ወኔያቸሁና ጀግንነታችሁ አኩርቶናል፣ እናመሰግናለን፣ ሁሌም ከጎናችሁ ነን” የሚል ምልእክት አስተላልፈዋል።

የግብርና ሚኒስቴር እና የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት አመራሮች እና ሠራተኞችም “ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ” መርሃ ግብር ለመከላከያ ሰራዊታ ያላቸውን ክብር ገልፀዋል።

የትምህርት ሚኒስቴርም “ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ክብር እቆማለሁ” ጥሪን ተቀብሎ የሁለት ደቂቃ የድጋፍ ስነ ስርዓት አካሂዷል።

የሚኒስትሩ አመራሮች እና ሰራተኞች ለአንድ ደቂቃ ቀኝ እጃቸውን ደረታቸው ላይ በማድረግ እና ለአንድ ደቂቃ ደግሞ በማጨብጨብ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ያላቸውን አጋርነት ገልፀዋል።

የሳይንስና ከፍተኛ  ትምህርት ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎችና  ሰራተኞች   “ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ክብር እንቆማለን” በሚል መሪ ቃል “ መከላከያ  ጥቃት የኛ ጥቃት ነው፣ የተቃጣውን ጥቃት እናወግዛለን፣ መከላከያ ሠራዊታችንን በምንችለዉ ሁሉ  እንደግፋለን”  በማለት ድጋፋቸውን ገልጸዋል።

የኢፌድሪ ማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞችም “ለሃገሬ የመከላከያ ሰራዊት ክብር እቆማለው!” ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ያላቸውን ክብርና ድጋፍ ገልጸዋል።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ አመራርና አባላት “ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ” መርሃ ግብር ላይ በመሳተፍ ለጀግናው የመከላከያ ሰራዊት ያላቸውን ክብርና ድጋፍ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አመራሮች እና ሰራተኞችም በመርሃ ግብሩ ላይ በመሳተፍ ለመከላከያ ሰራዊት ያላቸውን አጋርነት እና ክብር አሳይተዋል።