የሀገር ውስጥ ዜና

የተፈናቀሉ ወገኖችን ወደ ቀያቸው የመመለስና መልሶ የማቋቋም ስራው ተጠናክሮና መቀጠል ይገባዋል ተባለ

By Meseret Demissu

November 17, 2020

አዲስ አበባ፣ ህዳር 8 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሚመራው የሰብዓዊ ድጋፍ ቡድን በጥፋት ቡድኑ ላይ እየተደረገ ካለው የህግ ማስከበር እንቅስቃሴ ጎን ለጎን የተፈናቀሉና ከሃገር ውጭ የተሰደዱ ወገኖችን ወደ ቤታቸው የመመለስና መልሶ የማቋቋም ስራውን አጠናክሮና በተቀናጀ መልኩ መቀጠል ይገባል ሲል ገለፀ፡፡

ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል እንዳሉት ድጋፉ ከመከላከያ ሰራዊትና ሌሎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅርበት በመተባበር እንደ ሁኔታው አስቸኳይነት በፍጥነት መተግበሩን እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

ሚኒስትሯ ጉዳዩ ፋታ የሚሰጥ ስላልሆነ ከፍተኛ ርብርብ እንደሚፈልግ ተናግረዋል።

እንዲሁም የተሰደዱና የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ የማቋቋሙ ስራ ላይ ፈጣንና የተደራጀ እንቅስቃሴ  የሚደረግበትን አቅጣጫ ማስቀመጣቸውን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡