የሀገር ውስጥ ዜና

ምክትል ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

By Tibebu Kebede

November 18, 2020

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይታቸው ወቅትም በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ ለፕሬዚዳንቱ ገለጻ አድርገውላቸዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ በበኩላቸው በኢትዮጵያ በፍጥነት ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡