የሀገር ውስጥ ዜና

አህመድ አሊሚራህ አንፍሬ ህዋሓት በሰሜን ዕዝ ላይ የፈጸመውን ጥቃት አወገዙ

By Abrham Fekede

November 19, 2020

አዲስ አበባ ፣ህዳር 10 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አሕመድ አሊ ሚራህ አንፍ ህወኃት በሰሜን ዕዝ ላይ የፈጸመውን ጥቃት በአፋር ህዝብ ስም እንደሚያወግዙ ገለጹ፡፡

አሕመድ አሊሚራህ በወጣትነታቸው ደርግን ለሰባት ዓመታት መታገላቸውን አስታውሰው ደርግ ከተወገደ በኋላ ህወሓት የህዝቡን ትግል ለግል ጥቅሙ በሚመቸው መልኩ ማዋሉን ገልጸዋል፡፡

በዚህ አግላይ በሆነ ስርዓት ውስጥ ላለመሳተፍ ወስነው መቆየታቸውንም አስታውሰዋል፡፡

ባለፉት ዓመታትም ህወሓት በሀገሪቱ ሰላም እንዳይሰፍን ሲሰራ እንደነበርም አንስተዋል፡፡

አሁን እየተካሄደ ባለው ህግ የማስከበር ዘመቻም የትግራይ ህዝብ ለግል ጥቅሙ ለቆመው የህወሓት ቡድን እንደማይታገልም ነው የገለጹት፡፡

አህመድ አሊሚራህ እንደገለጹት የአፋር ህዝብ ታሪክ እንደሚያስረዳው የሀገር ሉዓላዊነትን በማስከበር የሚታወቅ ነው ብለዋል፡፡

በመጨረሻም ህዝቡ በጋራ በመረባረብ በህወሓት ላይ የተጀመረውን ህግ የማስከበር ዘመቻ ዳር እንዲያደርስ ጠይቀዋል፡፡