አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የህዝቦች አንድነትና እኩልነት እንዲረጋገጥ የትግራይ ህዝብ ፅኑ ፍላጎት እንዳለው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ ገለጹ።
ዶክተር አብርሃም በመላው ትግራይ አዲስ የፖለቲካ አስተሳሰብና ባህል እንዲያብብ ሁሉም ትግራዋይ የራሱ ድርሻ ሊኖረው የግድ ነው ብለዋል በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባጋሩት መረጃ።
የአበርክቶ ሚናውንም ሊጫወት ይገባል ነው ያሉት።
ጥላቻና ፍረጃ የሀሳብ ድርቀት ያጋጠማቸው የፈሪዎች አካሄድ ነው ሲሉም አስፍረዋል።
እንዲሁም ይህ አካሄድ ጥላቻና ፍረጃ ከፈጠረው ጋር አብሮ ሊያከትምለት ይገባል ነው ያሉት።