የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ የብሄራዊ የጀግኖችና የህጻናት አምባን የቦርድ አባላት አነጋገሩ

By Abrham Fekede

December 04, 2020

አዲስ አበባ፣ ህዳር 25፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ብሄራዊ የጀግኖችና የህጻናት አምባን የቦርድ አባላት ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

የቦርዱ አባላት ማህበሩ የተጎዱ ጀግኖችንና ቤተሰቦቻቸውን ለመርዳትና ለመንከባከብ የተቋቋመ ነው ብለዋል፡፡

አባላቱ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ የማህበሩ የበላይ ጠባቂ እንዲሆኑም ጠይቀዋል፡፡

በዚሁ ወቅት ፕሬዚዳንቷም የማህበሩ ዓላማ የተቀደሰና በጣም አስፈላጊ መበረታታት ያለበት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

“ጀግኖችን መንከባከብ የማህበረሰብ ግዴታ ነው” በማለትም የበላይ ጠባቂነት ጥያቄውን መቀበላቸውን ከፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!