አዲስ አበባ፣ ህዳር 27፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ሽረ ከተማ በአሁኑ ሰዓት ሰላማዊ እንቅስቃሴ መኖሩን በቦታው የሚገኙ የሰላም ሚኒስቴር የሰላምና ሰብዓዊ ድጋፍ ቡድን አባላት ገልጸዋል።
ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተጠሪ ተቋም የአደጋና ስጋት መከላከል ኮሚሽን ባልደረቦች ጋር በምዕራብ ግንባር በአካል በመገኘት ሰብዓዊ ድጋፍ በማስተባበር ላይ ይገኛሉ።
ጄኔራል ብርሀኑ ጥላሁን በሰሜን ዕዝ የምዕራብ ግንባር የሎጅስቲክስ ኃላፊ እንዳሉት የሽረ ከተማ እንቅስቃሴ ሰላማዊና ስትሆን ማህበረሰቡ ያለስጋት እየተንቀሳቀሰ እና የዕለት ተዕለት ተግባሩን እያከናወነ ነው፡፡
አክለውም በህግ ማስከበሩ ሂደት ለተፈናቀሉና ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች እየተደረገ ያለው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡
ጄኔራል ብርሀኑ ጦርነት አይበጅም ብለው ጠላትን በማሳፈር ከመከላከያ ሠራዊት ጎን ለቆሙ የትግራይ ህዝብና እንዲሁም ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ በተገኘው ድል የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ሀገርን በታላቅነቷ ለማስቀጠል ህግን የማስከበርና የሀገር ህልውና ዘመቻ ላይ ለተደረገው እና እንዲሁም እየተደረገ ላለው ከፍተኛ ርብርብና ድጋፍ እናመሰግናለንም ነው ያሉት፡፡
በሂደቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች መነሻውን አዲስ አበባ ያደረገ የዕለት ደራሽ ሰብዓዊ ድጋፍ ወደ ሽረ ከተማ እየገባ እንደሚገኝም ጠቅሰዋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!