አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 3፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በደርግ ዘመነ መንግስት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት ፍቅረስላሴ ወግደረስ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ።
የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሻምበል ፍቅረስላሴ በዛሬው ዕለት ነው በ75 ዓመታቸው ህይወታቸው ያለፈው።
ሻምበል ፍቅረስላሴ ወግደረስ አየር ኃይልን በመወከል ደርግን ከመሠረቱት ሰዎች መካከል አንዱ ሲሆኑ በኋላም ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩ ናቸው።
ሻምበል ፍቅረስላሴ ከረጅም የእስር ህይወት በኃላ “እኔና አብዮቱ” እና “እኛና አብዮቱ” የተባሉ ሁለት መፅሀፍትን ለአንባቢያን አቅርበዋል ።
ፍቅረስላሴ ወግደረስ የተወለዱት ሐምሌ 7 ቀን 1937 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሲሆን በኢትዮጵያ አየር ኃይል ማሰልጠኛ ወጣት ካዴት ሆነው በመግባት በ1955 ዓ.ም የተመረቁ ሲሆን በአሜሪካ ሀገርም ስልጠና ወስደዋል።
በተለያዩ የስልጣን እርከኖች ሀገራቸውን ያገለገሉት ፍቅረስላሴ የኢትዮጵያ ሰራተኞች ፓርቲ (ኢሰፓ) አደራጅ ኮሚቴና የደርግ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል እና ከጳጉሜን 5 ቀን 1979 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 29 ቀን 1982 ዓ.ም የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን አገልግለዋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!