አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጤና ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ የተመራ ከጤና ሚኒስቴር እና ኢንጀንደር ሄልዝ የተውጣጣ የስራ ኃላፊዎች ቡድን በደቡብ ክልል የሚገኙ የጤና ተቋማትን ጎበኘ።
ቡድኑ በክልሉ በሐዲያ፥ ወላይታና ጋሞጎፋ ዞኖች በሚገኙ የጤና ተቋማት ለሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት አድርጓል።
በሐዲያ ዞን የሾኔ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል፣ ቆርጋ ጤና ጣቢያ፣ በወላይታ ዞን የወላይታ ሶዶ ማስተማሪያ ሆስፒታል እና በጋሞ ጎፋ ዞን የአርባ ምንጭ ጠቅላላ ሆስፒታልን ተጎብኝተዋል።
ኢንጀንደር ሄልዝ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በተለይም በቤተሰብ እቅድና ስነ ተዋልዶ ጤና ላይ የሰራቸው ስራዎች አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡን የጤና ሚኒስትር ዲኤታው ዶክተር ደረጀ ዱጉማ ገልጸዋል።
ውጤቱ በተለያዩ ደረጃ የሚገኙ አመራሮች፣ የጤና ባለሙያዎችና አጋር ድርጅቶች በቅንጅት መስራት በመቻላቸው ሊገኝ መቻሉን በጉብኝቱ የተሳተፉ የስራ ኃላፊዎች ተናግረዋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!