የሀገር ውስጥ ዜና

የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጀኔራል ይልማ መርዳሳ የምዕራብ አየር ምድብን ጎበኙ

By Tibebu Kebede

December 21, 2020

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጀኔራል ይልማ መርዳሳ የምዕራብ አየር ምድብን ጎበኙ፡፡

በጉብኝታቸው ወቅትም የምድቡ ሰራዊት ከሀዲው ያሴረውን ሀገርን የማተራመስ እቅድ ለማክሸፍ አመራሩ በጥበብ አባላቱም በጀግንነት ውሎ ለፈፀሙት አኩሪ ገድል በማመስገን ጀግኖች ናችሁ ብለዋል።

የምዕራብ አየር ምድብ የሕወሓት ጁንታ ሴራን ለማክሸፍ በተደረገው የህግ ማስከበር ዘመቻ ታላቅ ተጋድሎ እንደፈጸመ ማረጋገጣቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የሀገር መከታ በሆነው የመከላከያ ሠራዊት ላይ ሰው በላው ቡድን የራሱን ጓድ ከኋላው ሆኖ በመውጋቱ አባላቱ የገጠማቸውን ልብ የሚሰብር ሀዘን ችለው የምድቡ አመራርና አባላት ቅንጅት በመፍጠር በሀገራዊ ሞራልና ስሜት የሕዝብ ልጅ መሆናቸውን በተግባር ማስመስከራቸውንም ጠቅሰዋል፡፡

በቀጣይም የቴክኖሎጂ አቅም እና ክህሎትን በማሳደግና የሰው ሀይልን በስልጠና በማብቃት፣ ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አስተሳሰብ ፍፁም ነፃ በመሆን የሪፎርም አደረጃጀቱን ይበልጥ በማጠናከር የሀገር መከታነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥልም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!