የሀገር ውስጥ ዜና

የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቋል

By Tibebu Kebede

January 04, 2020

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ትናንት ሲያካሂድ የነበረውን የመጀመሪያ ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ አጠናቋል።

ፓርቲው ከግንባር ወደ ውህድ ፓርቲ ከተሸጋገረ በኋላ ባካሄደው የመጀመሪያ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባም በተለያዩ ወቅታዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ መምከሩ ተገልጿል።