አዲስ አበባ፣ታህሳስ 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ከሰሞኑ ወደ ኢትዮጵያ የገባው መጠነኛ እርጥበት አዘል አየር በአንዳንድ አካባቢዎች መጠነኛ ዝናብ እንዲኖር የሚያደርግ በመሆኑ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ የብሄራዊ ሜቲዮሮሎጂ ኤጀንሲ አሳሰበ።
በኤጀንሲው የትንበያ እና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ዳይሬክተር ወይዘሮ ጫሊ ደበሌ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት÷አሁን ላይ በቀን ደረቅና ነፋሻማ አየር በሌሊት እንዲሁም ማለዳ ላይ ቅዝቃዜ የሚጠበቅ ቢሆንም እርጥበት አዘል አየር ወደ ሃገር ውስጥ በመግባቱ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ ደመናማ እና አልፎ አልፎ ዝናብ እየተስተዋለ ነው።
ይህም ከህንድ ውቅያኖስ ወደ ኢትዮጵያ የገባው ቀዝቃዛ አየር በመካከለኛው የኢትዮጵያ አካባቢዎች ደመና በመፍጠር ዝናብ አስከትሏል ነው ያሉት። የአየር ሁኔታው ደመናማ እና አልፎ አልፎ ዝናብ መጣሉ አሉታዊ እና አዎንታዊ ተጽዕኖ ሊያስከትል እንደሚችልም ገልፀዋል።
በዚህም በደረሱ ሰብሎች እና በድህረ ሰብል ስብሰባው ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያስከትል ስለሚችል አርሶ አደሮች ተገቢውን ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል ነው ያሉት።
እርጥበቱና ዝናቡ በደረሱ ሰብሎች ላይ ሊያስከትል ከሚችለው ጉዳት ባሻገርም በጓሮ አትክልቶች እና ለቋሚ ሰብሎች ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል ብለዋል።
በቀጣይ ከጥቂት ቀናት በኋላ ወደ ሃገር ውስጥ የሚገባው እርጥበት አዘል አየር የሚቀንስ በመሆኑ በተፈጠረው ደመና የሌሊቱ እና የማለዳው ቅዝቃዜ ጋብ እንደሚል እንደሚጠበቅ ዳይሬክተሯ ተናግረዋል፡፡
በበላይ ተስፋዬ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!