አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ትምህርት በተጀመረባቸው አካባቢዎች ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት እንዲልኩ የትምህርት ሚኒስቴር ጥሪ አቀረበ።
የኮቪድ 19 ወረርሽኝን በመከላከል የመማር ማስተማር ስራው ቢጀመርም በርካታ ተማሪዎች በትምህርት ገበታቸው ላይ መገኘት አልቻሉም ተብሏል።
በዚህ ጉዳይ ላይ የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች በበይነ መረብ ተወያይተዋል።
በዚህ ወቅትም ተቋርጦ የነበረው የመማር ማስተማር ስራ ድጋሚ የተጀመረ ሲሆን አሁንም ወደ ትምህርት ገበታቸው ያልተመለሱ ተማሪዎች እንዳሉ ተነስቷል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት እንዲልኩ ጥሪ አቅርበዋል።
ትምህርት ላይ የሚሰሩ አጋር አካላትና ከትምህርት ዘርፍ ውጭ ያሉ ተቋማትም ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ እየተደረገ ያለውን ጥረት እንዲደግፉ ጠይቀዋል።
“ወደ ትምህርት ቤት እንመለስ” በሚል ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታቸው የመመለስ ዘመቻ እንደሚጀመርም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!