የሀገር ውስጥ ዜና

ተጨማሪ 410 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 1 ሺህ 21 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል

By Tibebu Kebede

December 24, 2020

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰአታት ለ5 ሺህ 503 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 410 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ባለፉት 24 ሰአታት ውስጥ የ12 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ሳቢያ ሲያልፍ 1 ሺህ 21 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል።

በዚትዮጵያ እስካሁን 121 ሺህ 399 ሰዎች ቫይረሱ ሲገኝባቸው ከዚህ ውስጥ 106 ሺህ 845 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል።

አሁን ላይም 12 ሺህ 670 ሰዎች ቫይረሱ ያለባቸው ሲሆን ከእነዚህ ውስጥም 236 ሰዎች በጽኑ ህክምና ላይ ይገኛሉ ብሏል።

በኢትዮጵያ በቫይረሱ ሳቢያ እስካሁን 1 ሺህ 882 ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!