የሀገር ውስጥ ዜና

ከታሪክ ሳይማሩ በእሳት መጫወት አዙሪት ውስጥ ስለሚከተን ተቀናጅተን እንስራ -ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ

By Tibebu Kebede

December 24, 2020

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በበኒሻንጉል ጉሙዝ መተከል ዞን በንጹሀን ዜጎች ላይ በደረሰው የህይወት ህልፈትና አካል ጉዳት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ።

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ሞትን በፍጹም መላመድ የለብንም ብለዋል።

በመተከል በንጹሃን ዜጎች፥ ሴቶች፥ ሕጻናት እና ቤተሰብ ላይ በየጊዜው የሚፈጸሙ ግድያ በጽኑ የሚወገዝ ነው ማለታቸውን ከፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ከታሪክ ሳይማሩ በእሳት መጫወት አዙሪት ውስጥ የሚከተን ስለሆነ ተቀናጅተን እንድንሰራ በአደራ ጭምር እጠይቃለሁ ብለዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!