A nurse from Lancet Nectare hospital waits for the next patient to perform a COVID-19 coronavirus test during in Richmond, Johannesburg, on December 18, 2020. (Photo by LUCA SOLA / AFP)

ዓለምአቀፋዊ ዜና

በደቡብ አፍሪካ በኮሮና የተያዙ ሰዎች ቁጥር 1 ሚሊየን አለፈ

By Meseret Awoke

December 28, 2020

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ አፍሪካ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ1 ሚሊየን መብለጡ ተገልጿል፡፡

በሃገሪቱ አዲስ የኮሮና ቫይረስ መገኘቱ ከተረጋገጠ ቀናት በኋላ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር ከ1 ሚሊየን 4 ሺህ 400 በላይ መድረሱን የሃገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

እስካሁን በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥርም ከ26 ሺህ 700 በላይ ሆኗል፡፡

በርካታ ሆስፒታሎች እና የህክምና ማዕከላት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ታማሚዎች ለማከም የበዓላትን ቀናት በመሰረዝ የጤና ባለሙያዎች በስራ ገበታቸው እንዲገኙ አድርገዋል፡፡

ከአዲሱ የቫይረሱ ዝርያ ጋር በተያያዘም በርካታ ሃገራት ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚያደርጉትን በረራ የሰረዙ ሲሆን ለደቡብ አፍሪካ ዜጎችም ወደ ሃገራቱ መግባት የተከለከለ ነው፡፡

በአፍሪካ ቫይረሱ ከጸናባቸው ሃገራት መካከል ደቡብ አፍሪካ በቀዳሚነት ስትጠቀስ ሞሮኮ፣ ግብጽ፣ቱኒዚያ እና ኢትዮጵያ ይከተላሉ፡፡

እስካሁን በዓለም ዙሪያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ81 ሚሊየን በላይ ሲሆን፤ በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥርም ከ1 ሚሊየን 772 ሺህ በላይ ሆኗል፡፡

በአንጻሩ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ከ57 ሚሊየን 304 ሺህ በላይ ሆኗል፡፡

ምንጭ፡- አልጀዚራ እና ዎርልድ ኦ ሜትር