አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአቶ ሴኩቱሬ የልጅ ባል አብነት ሃይሉሸዋ በፌደራል ፖሊስ በዋስ እንዲፈታ ተደረገ፡፡
ግለሰቡ ከህወሓት ፀረ ሰላም ቡድን ጋር ግንኙነት አለው በሚል ተጠርጥሮ ምርመራ ሲደረግበት መቆየቱ ይታወሳል፡፡
ይሁንና ተጠርጣሪው በምስክርነት ዞሮ በዋስ እንዲወጣ የተደረገ ሲሆን ከሃገር እንዳይወጣ እግድ መጣሉንም ማወቅ ተችሏል፡፡
በሌላ በኩል በማይካድራ የአማራ ተወላጆች መገደል አለባቸው እያለች ስታስተባብር ነበር የተባለችው ወታደር ሃጎስ ገብረትንሳይ ጉዳይዋ በመከላከያ የጦር ፍርድ ቤት እንዲታይ መዝገቡ ወደ መከላከያ የጦር ፍርድ ቤት ዞሯል፡፡
ተጠርጣሪዋ ከዚህ ቀደም በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራድ ምድብ ከዚህ በፊት ቀርባ ጉዳይዋ መታየቱ የሚታወስ ነው፡፡
በታሪክ አዱኛ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!