አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ቱሪዝም ኢትዮጵያ በሰባት የተለያዩ የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎች ልዩ የኢንቨስትመንት ማበረታቻ ማድረጉን አስታወቀ።
ልዩ ማበረታቻ የተደረገላቸው መዳረሻዎች አብጃታ ሻላ ሐይቆች፣ ባሌ ተራሮች፣ ወንጪ ሐይቅ፣ ገርዓልታ ተራራ፣ ሰሜን ተራሮች፣ ነጭ ሳር እና ኤርታሌ ናቸው።
የቱሪዝም ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር አቶ ስለሺ ግርማ በኢትዮጵያ ለ3 ሺህ ዓመታት በዘለቀው የግብርና ስራ ህዝቡ ከድህነት መውጣት አልቻለም ያሉ ሲሆን ÷ የኢንዱስትሪ ዘርፉም እስካሁን በሚፈለገው መጠን ውጤታማ ሳይሆን መዝለቁን ጠቅሰዋል።
የቱሪዝም ዘርፉን በማልማት የህዝቡን ኑሮ መቀየርና ኢትዮጵያን ማሳደግ እንደሚቻል አመልክተዋል።
የቱሪዝም ዘርፍ ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራበት መሆኑን ጠቁመው ÷ ቱሪዝም ኢትዮጵያም ሰባት የቱሪስት መዳረሻዎችን ለማልማት ልዩ የኢንቨስትመንት ማበረታቻዎችን መፍቀዱን ተናግረዋል።
ይህም በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ቦርድ መጽደቁን የተናገሩ ሲሆን÷ልዩ ማበረታቻዎቹ ከውጭ አገር ግብዓት ከቀረጥ ነጻ ማስገባትን ጨምሮ ለ5 ዓመታት የግብር እፎይታን አካቶ የያዘ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!