የሀገር ውስጥ ዜና

ህብረተሰቡ በኮሮና ቫይረስ መከላከል ላይ እያሳየ ያለው መዘናጋት ሊቆም ይገባል –  አቶ ርስቱ

By Tibebu Kebede

December 30, 2020

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የኮሮና ቫይረስ እየተስፋፋ መምጣቱን ተከትሎ በህብረተሰቡ ዘንድ እየታየ ያለው መዘናጋት ሊቆም እንደሚገባ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ሀገር አቀፍ የአፋጣኝ ጊዜ የኮሮና ቫይረስ መከላከል እና መቆጣጠር ተግባራት አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።

በክልሉ ከዚህ በፊት የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ይወሰድ የነበረው ጥንቃቄ በአርአያነቱ የሚጠቀስ ነበር ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ አሁን ግን የቫይረሱ የስርጭት መጠን እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ  ህብረተሰቡ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት ብለዋል፡፡

በክልሉ በተለያዩ ተቋማት አልግሎት ሰጪ አካላት የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል እንዲጠቀሙ ማድረግ ይገባቸዋል ብለዋል።

አቶ ርስቱ ተገልጋዩ ህብረተሰብም ማስክ ሳያደርግ ወደ ተቋማት መሄድ የለበትም ብለዋል፡፡

በክልሉ ከ4 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በቫይረሱ መያዛቸውን ጠቁመው 46 ዜጎች ደግሞ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ማለፉን መናገራቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽ ጉዳዮች ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ከዚህ ቀደም ወጣቶች በሽታውን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር  ሲያከናውኑት ለነበረው የበጎ ፈቃድ ስራ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ አቅናው ካውዛ እንደገለጹት በክልሉ የቫይረሱ ስርጭት አስከፊ ደረጃ ላይ እየደረሰ ነው፡፡

አቶ አቅናው በክልሉ ከ150 ሺህ በላይ ምርመራ የተደረገ ሲሆን ከ4 ሺህ በላይ ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡

በክልሉ የመካኒካል ቬንትሌተር በቂ አለመሆኑን የተናገሩት አቶ አቅናው አስከፊ ሁኔታ ከመፈጠሩ በፊት በህብረተሰቡ ዘንድ የሚታየው መዘናጋት መቆም እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!