አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ለተማሪዎች የኮቪድ19 ስልጠና ሰጠ።
ዩኒቨርሲቲው ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመሆን በዩኒቨርሲቲው ለሚማሩ ተማሪዎች በመማር ማስተማር ሂደት ላይ እና ተማሪዎች የተሻለ ስነ ልቦና እንዲገነቡ የሚያስችላቸውን ስልጠና ነው የሰጠው።
የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሳላህ ሁሴን በስልጠናው መክፈቻ ላይ በኮቪድ 19 ምክንያት ተቀቋርጦ የነበረው ትምህርት አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ መጀመሩን ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቅትም 2 ሺህ 170 ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ትምህርት መጀመራቸው ነው የተገለጸው።
ከዚህ ባለፈም በመግቢያዎች ላይ ሊደረጉ የሚገቡ ጥንቃቄዎች በአንድ ክፍል ሊስተናገዱ የሚገባቸው ተማሪዎች ቁጥር እና የዶርም ጥምርታ ላይ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር መስፈርት መሰረት እየተስተናገዱ እንደሚገኝ ተነግሯል።
ዩኒቨርሲቲው ከዚህ በፊት ከ33 ሺህ በላይ ተማሪዎችን በተለያየ የመደበኛ፣ ተከታታይና ርቀት ትምህርት ፕሮግራም አስተምሮ አስመርቋል፡፡
ኮቪድ19 ከመግባቱ በፊት 28 ሺህ ተማሪዎችን በተለያየ ፕሮግራም ሲያስተምር እንደነበር ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!