የሀገር ውስጥ ዜና

የዲክኒል – ዳጉር መንገድን ከ43 ሚሊየን ዶላር በላይ በሆነ ወጪ ለመገንባት ስምምነት ተፈረመ

By Abrham Fekede

January 01, 2021

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 23፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን የዲክኒል – ዳጉር መንገድን ከ43 ሚሊየን ዶላር በላይ የኮንትራት ዋጋ የዲዛይንና የግንባታ ስራ ለማከናወን ከጂቡቲ ወደቦች ኮሪደር ጋር ተፈራረመ፡፡

የኮንትራት ስምምነቱን የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ዮናስ አያሌው እና የጂቡቲ ወደቦች ኮሪደር ዋና ዳይሬክተር አብዲ ኢብራሂም ፋራህ ጋር ተፈራርመዋል፡፡

የዲክኒል – ዳጉር የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት 80 ኪሎ ሜትር ርዝመት አለው ተብሏል፡፡

35 ኪሎ ሜትሩ በአስፓልት ኮንክሪት ሲሸፈን ቀሪው 45 ኪሎ ሜትር ደግሞ የጠጠር መንገድ ጥገና መሆኑ ተገልጿል፡፡

የከኢትዮ-ጂቡቲ ድንበር 20 ኪሎ ሜትር ወደ ጂቡቲ ገባ ብሎ የሚጀምረው ይህ የመንገድ ዲዛይንና ግንባታ ፕሮጀክት የግንባታ ስራው በስምንት ወራት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!