የሀገር ውስጥ ዜና

በቡራዩ 4 የእጅ ቦምብ እና 1 ፈንጂ ተያዘ

By Tibebu Kebede

January 11, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በቡራዩ ከተማ አስተዳደር 4 የእጅ ቦምብ እና 1 ተቀጣጣይ ፈንጂ ተያዘ።

ህገወጥ የጦር መሳሪያው በህብረተሰቡ ጥቆማ በገፈርሳ ቡራዩ ቀበሌ ነው የተያዘው።

ፖሊስ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ባደረገው ክትትል ህገወጥ የጦር መሳሪያው መገኘቱን አስታውቋል።

በከተማዋ በአንድ ወር ውስጥ ብቻ 12 ክላሽ፣ 10 የእጅ ቦምብ እና 2 ፈንጂ በቁጥጥር ስር መዋሉን የቡራዩ ከተማ አስተዳደር ኮሙዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ገልጿል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!