የሀገር ውስጥ ዜና

በ’ገበታ ለሀገር’ ለመሳተፍ ገንዘብ ገቢ ላደረጉ እና ላሳወቁ የሰባተኛ ዙር ተቋማት ምስጋና ቀረበ

By Tibebu Kebede

January 12, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በ’ገበታ ለሀገር’ ለመሳተፍ ገንዘብ ገቢ በማድረግ የባንክ ደረሠኝ በመላክ ያሳወቁ የሰባተኛ ዙር ተቋማትን ይፋ አደረገ::

ጽሕፈት ቤቱ ገንዘብ ገቢ ላደረጉ እና ደረሠኙን በመላክ ላሳወቁ የሰባተኛ ዙር ተቋማት ምስጋና አቅርቧል። በዚህም መሰረት፡-

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርት ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት – 30 ሚሊየን ብር

የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምሕርት ሚኒስቴር ማኅበረሰብ – 130 ሚሊየን ብር

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ – 40 ሚሊየን ብር

ዲ.ኤች. ገዳ ንግድ እና ኢንደስትሪ – 5 ሚሊየን ብር

ብርሀንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት – 5 ሚሊየን ብር

ትራንስፖርት ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማቱ – 35 ሚሊየን ብር

ኢትዮ ቴሌኮም – 350 ሚሊየን ብር ሲሆን

ሌሎች ተሳታፊ ተቋማትም የ5 እና የ10 ሚሊየን ብር አስተዋጾአቸውን ባንክ ያስገቡበትን ደረሰኝ በdineforethiopia@pmo.gov.et መላክ እንደሚችሉ የጠ/ሚ ጽ/ቤት አስታውቋል ።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!