የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ መላኩ አለበል ከቱርክ የንግድ ሚኒስትር ረሽሳስ ፔካን ጋር መከሩ

By Tibebu Kebede

January 15, 2021

አዲስ አበባ ፣ ጥር 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ከቱርክ የንግድ ሚኒስትር ረሽሳስ ፔካን ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መከሩ።

በቆይታቸው የሁለቱ ሀገራት የንግድ ልውውጥ ዙሪያ ተወያይተዋል።

ኢትዮጵያ ከሁለት አመት በፊት በቱርክ ለወጪ ንግድ ከተመረጡ 17 ሀገራት መካከል አንዷ መሆኗ ይታወቃል።

እንደ ቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ በፈረንጆቹ 2019 የሁለቱ ሀገራት የንግድ ልውውጥ 398 ነጥብ 8 ሚሊየን ዶላር ደርሷል።

ከዚህ ውስጥ ቱርክ ወደ ኢትዮጵያ የምትልከው የምርት መጠን 378 ነጥብ 3 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር መሆኑ ተገልጿል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!