የሀገር ውስጥ ዜና

የደቡብ ክልል ምክር ቤት ቀጣዩን ምርጫ በሚመለከት የምክር ቤት ተወካዮችን ብዛት የሚወስን አዋጅ አጸደቀ

By Tibebu Kebede

January 15, 2021

አዲስ አበባ ፣ ጥር 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ምክር ቤት ቀጣዩን ምርጫ በሚመለከት የምክር ቤት ተወካዮችን ብዛት የሚወስን አዋጅን አጽድቋል።

ምክር ቤቱ ዛሬ በካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ በተለይም ክልሎች በየደረጃው የሚገኙ የምክር ቤት አባላትን ብዛት እና በአንድ የምርጫ ክልል ወይም አካባቢ ምን ያህል ተወካዮች እንደሚመረጡ በህግ ሊወሰን የሚገባ በመሆኑ አዋጁ አስፈልጓል ብሏል።

በአዲሱ አዋጅ መሰረት በክልል ምክር ቤት አባላት ምርጫ በአንድ የምርጫ ክልል 5 ተወካዮች ለዞን ምክር ቤት፣ 7 እና ከዚያ በታች ወረዳ ባላቸው 10 ተወካዮች፣ ከ7 በላይ ወረዳ ባላቸው 5 ተወካዮች፣ ለወረዳ ምክር ቤት ከየቀበሌው 5 ተወካዮች፣ ለከተማ አስተዳደር ከየቀበሌው 5 ተወካዮች፣ ለፈርጅ 1 ከተማ ከየቀበሌው ከ10 እስከ 15 ተወካዮች፣ ለፈርጅ 2 ከተማ ከየቀበሌው ከ20 እስከ 30፣ ለፈርጅ 3 ከተማ፣ ለታዳጊ ከተማ አስተዳደር ከየቀበሌ 40 ተወካዮች እንዲሁም ለገጠርና ከተማ ቀበሌዎች 120 ተወካዮች እንዲኖሩ ተደርጓል።

በክልሉ 106 መደበኛ የምርጫ ክልሉችና ነባር ከነበሩት 18 ልዩ የምርጫ ጣቢያዎች 9 ተጨምረው 27 ልዩ የምርጫ ጣቢያዎች ይኖራሉ ተብሏል፡፡

በብርሃኑ በጋሻው ፤ ተጨማሪ መረጃ ከደቡብ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!