አዲስ አበባ ፣ ጥር 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳ በጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ የሚገኘውን የጎቼ ጅብ የመስኖ ፕሮጀክት ጎበኙ፡፡
ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ፕሮጀክቱን በጎበኙበት ወቅት የመስኖ ግንባታው እንዲጠናቀቅ ህብረተሰቡ ላደረገው ድጋፍ አመስግነዋል፡፡
የተጀመረው ልማት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ያቀረቡት አቶ ርስቱ አካባቢውን ለማልማት የሚደረገውን ጥረት የክልሉ መንግሥት እንደሚደግፍ ተናግረዋል፡፡
በመስቃን ወረዳ ሚካኢሎ ቀበሌ ከ27 ሚሊየን በላይ ብር ግንባታው እየተጠናቀቀ ያለው የጎቼ ጅብ የመስኖ ፕሮጀክት 246 አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያመለክታል።
በመስቃን ወረዳ ከ50 ሄክታር በላይ መሬት እንደሚያለማ የሚጠበቀው ፕሮጀክቱ 90 በመቶ መጠናቀቁ ነው የተነገረው፡፡
በጉብኝቱ የወረዳው አርሶ አደሮች እንደገለጹት አካባቢው ለምና ለእርሻ ስራ ምቹ በመሆኑ ከመስኖ ልማት ስራ ተጠቃሚ ለመሆን አቅደው እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!