አዲስ አበባ ፣ ጥር 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የዓለም ዓቀፉ የትምህርት ስርአት የወደፊት ሁኔታ ላይ ለመምከርና ለማቀድ የተቋቋመውን ኮሚሽን ሰበሰቡ፡፡
ከመላው ዓለም የተውጣጡ ምሁራንንና ባለሙያዎችን ያቀፈው ኮሚሽኑ ለወደፊት ዘመናዊ እና ሁሉን አቀፍ ትምህርት ምን መምሰል እንዳለበት ለፖሊሲ አውጭዎች፣ ለአስተማሪዎችና ለተማሪዎች መመሪያ ሆኖ የሚያገለግል ሪፖርት እያዘጋጀ ነው፡፡
የኮሚሽኑ አባላት እስካሁን በተሰራው ስራ ላይ የተወያዩ ሲሆን፥ ሪፖርቱ በፈረንጆቹ 2021 መጨረሻ ይታተማል መባሉን ከፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኮሚሽኑ በፈረንጆቹ 2019 በኒውዮርክ በተዘጋጀው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ መመስረቱ የሚታወስ ነው፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!