የሀገር ውስጥ ዜና

በታህሳስ ወር ከ22 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

By Meseret Awoke

January 20, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በታህሳስ ወር ከ22 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው አስታወቁ፡፡

ሚኒስቴሩ በታህሳስ ወር 21 ቢሊየን 338 ሚሊየን 652 ሺህ 82 ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 22 ቢሊየን 375 ሚሊየን 335 ሺህ 266 ብር ገቢ መሰብሰቡን አስታውቀዋል፡፡

ይህም የእቅዱን 105 በመቶ መሆኑንም ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

ገቢው ከሀገር ውስጥ ገቢ፣ ከወጪንግድ ቀረጥና ታክስ እና ከሎተሪ ሽያጭ የተሰበሰበ ነው ተብሏል፡፡

የዘንድሮው ገቢ ካለፈው በጀት አመት አንፃር በ23 በመቶ ዕድገት እንዳለውም በፌስ ቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ አስታውቀዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!