አዲስ አበባ ፣ ጥር 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 41ኛው የአፍሪካ ህብረት አባል ሃገራት ቋሚ መልዕክተኞች መደበኛ ስብሰባ በቪዲዮ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው፡፡
ስብሰባው “ኪነ ጥበብ፣ ባህል እና ቅርስ የምንፈልጋትን አፍሪካ ለመገንባት” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ መሆኑን የህብረቱ መረጃ ያመላክታል፡፡
ከህብረቱ መሪዎች ጉባኤ ቀደም ብሎ የሚካሄደው ይህ ስብሰባ በተለያዩ አህጉራዊና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚወያይ ይጠበቃል፡፡
የቋሚ መልዕክተኞች ንዑስ ኮሚቴዎች የስራ እንቅስቃሴ፣ የልዩ ቴክኒካል ኮሚቴዎች ሪፖርት፣ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሪፖርት እና የህብረቱ ሌሎች የስራ ክፍሎች እና አካላት ያለፈው አመት የስራ ክንውንም የስብሰባው መወያያ አጀንዳ ይሆናል ተብሏል፡፡
ለሁለት ቀናት የሚካሄደው ስብሰባ ለህብረቱ የስራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት 38ኛ ስብሰባም የመወያያ አጀንዳ ያረቃል ተብሎም ይጠበቃል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!