የሀገር ውስጥ ዜና

በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን ጎበኙ

By Tibebu Kebede

January 20, 2021

አዲስ አበባ ፣ ጥር 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር ሬሚ ማሬሻ የቅዱስ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን ጎበኙ፡፡

በጉብኝታቸውም ስለ ቅርሱ አጠቃላይ ታሪክ፣ በየዘመናቱ ስለተደረጉ የተለያዩ የጥገና እና የጥበቃ ሥራዎች ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡

የጥገና እና የጥበቃ ስራዎቹ ቅርሱን እስከዛሬ ጠብቆ ለማቆየት የነበራቸው አወንታዊ ገጽታ እና አሉታዊ ጫናን በተመለከተም ዝርዝር ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል።

ከዚህ ጎን ለጎንም በአሁኑ ጊዜ በፈረንሳይ የሚደገፈው ፕሮጀክት የያዛቸው የጥበቃ፣ ጥገና እና ልማት ስራዎች የደረሱበትን ደረጃ በተመለከተ ማብራሪያ እንደተደረገላቸው ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!