የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ በላይነህ ክንዴ ከመተከል ዞን ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል 800 ኩንታል የምግብ እህል ድጋፍ አደረጉ

By Meseret Awoke

January 21, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) አቶ በላይነህ ክንዴ ከመተከል ዞን ተፈናቅለው በቻግኒ-ራንች ጊዜያዊ መጠለያ ለሚገኙ ተፈናቃዮች የ800 ኩንታል ዱቄት ድጋፍ ማድርጋቸው ተገለፀ፡፡

በቻግኒ ከተማ አስተዳደር በጊዜያዊነት የተቋቋመው የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት አስተባባሪ አቶ ጀምበሩ ደሴ እንደገለፁት አቶ በላይነህ ክንዴ የ800 ኩንታል ዱቄት ድጋፍ አድርገዋል፡፡

አስተባባሪው እንዳታወቁት ባለሃብቱ በላይነህ ክንዴ ያደረጉት ድጋፍ ለተፈናቃዮች ጊዚያዊ እፎይታ የሚሰጥ እና ለወገን ደራሽነታቸውን ያሳዩበት ነው ብለዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በቻግኒ ከተማ ራንች በተባለው ጊዜያዊ መጠለያ ከ40 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች እንዳሉ አስታውቀዋል፡፡

ድጋፉ 5 ሺህ 330 ተፈናቃዮችን ለአንድ ወር መመገብ የሚችል መሆኑን አብመድ ዘግቧል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!