የሀገር ውስጥ ዜና

የዘንድሮው 125ኛ የዓድዋ ድል በዓል ብሄራዊ አንድነትን በሚያጠናክር መልኩ ይከበራል – ዶ/ር ሂሩት ካሳው

By Meseret Demissu

January 21, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የዘንድሮው 125ኛ የዓድዋ ድል በዓልን ብሄራዊ አንድነትን በሚያጠናክር መልኩ ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶ/ር ሂሩት ካሳው እንደገለፁት በዓሉ የብሄራዊ አንድነት መገለጫ ነው፡፡

ኢትዮጵያ የጀመረችውን የብልፅግና ጉዞ በሚደግፍ መልኩ በዓሉ ይከበራልም ብለዋል፡፡

ሚኒስትሯ በሰጡት መግለጫ እንዳታወቁት 125ኛው የዓድዋ ድል “ህብረ ብሄራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል ይከበራል፡፡

የሁሉንም ህዝቦች አስተዋፅዖ በሚያጎለብት መልኩ በሁሉም የሀገሪቱ አከባቢዎች ይከበራል ነው ያሉት፡፡

በዝግጅቱ የስነ-ጥብ ስራዎች እና የተለያዩ ውይይቶችም ይካሄዳሉ ብለዋል::

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!