የሀገር ውስጥ ዜና

የምክንያታዊ ወጣቶች የውይይትና የሙግት መድረክ በደቡብ ክልል እየተካሄደ ነው

By Tibebu Kebede

January 22, 2021

አዲስ አበባ ፣ ጥር 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የምክንያታዊ ወጣቶች የውይይትና የሙግት መድረክ በደቡብ ክልል በሚገኙ የዞን ከተሞች መካሄድ ጀመረ፡፡

ለሁለት ቀናት የሚቆየው መድረክ በክልሉ በሚገኙ ስድስት ከተሞች እየተካሄደ መሆኑን የክልሉ ብልፅግና ወጣቶች ሊግ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

የምክንያታዊ ወጣት የውይይትና የሙግት መድረክ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳድርን ጨምሮ በተለያዩ ክልሎች ሲካሄድ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

መድረኩ በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች የተካሄደ ሲሆን 5 ሚሊየን ወጣቶችን የማሳተፍ እቅድ ያለው ነው፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!