የሀገር ውስጥ ዜና

በምዕራብ ወለጋ ዞን የባቦ ገምቤል ወረዳ ነዋሪዎች ኦነግ ሸኔን ተቃወሙ

By Tibebu Kebede

January 22, 2021

አዲስ አበባ ፣ ጥር 14 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በምዕራብ ወለጋ ዞን የባቦ ገምቤል ወረዳ ነዋሪዎች ኦነግ ሸኔን አወገዙ።

በባቦ ገምቤል ወረዳ የአምባሎ ዲላ ነዋሪዎች ቡድኑን በመቃወም ሰልፍ አካሂደዋል።

በሰልፉም የኦነግ ሸኔን የጥፋት ድርጊት እንቃወማለን ብለዋል።

ሰልፈኞቹ ኦነግ ሸኔ በአካባቢያቸው የልማት ስራ እንዳይሰራ እንቅፋት መሆኑን ገልጸዋል።

በቡድኑ ምክንያት በአካባቢያቸው ሰላም ማጣታቸውንም አስታውቀዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!