አዲስ አበባ ፣ ጥር 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሮፌሰሮች ምክር ቤት 2ተኛ መደበኛ ጉባኤውን አካሂዷል።
ምክር ቤቱ በጉዳኤው በቀጣይ የሚሰራቸው ተግባራቶችን የሚከታተሉ ቋሚ ኮሚቴዎች አቋቁሟል።
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለፕሮፌሰሮች ምክር ቤት ባስተላለፉት መልእክት ለሀገር እድገት የሚጠበቅባቸውን ሚና በጋራ ለመወጣት እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።
ምርምሮችን በጋራ በመስራት ለሀገር ተጨባጭ ውጤት እንዲያመጣ መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በተናጥል ሳይሆን በጋራ ከዳር ሳይሆን ከመሀል ሆናቹ ሀገራችሁን አሻግሩ ብለዋል።
ከዚህ በተጨማሪ የምርምር ጽሁፎችን አዘጋጅቶ ለአለም አቀፍፍ ማህበረሰብ በማቅረብ የኢትዮጵያን ገጽታ መገንባት እንደሚገባቸውም ፕሬዚዳቷ አንስተዋል።
70 አመታትን የተሻገረው የኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ 51 የመንግስትና 4 የግል ዩኒቨርሲቲዎችን ጨምሮ በርካታ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ተቋማትን መገንባት ችሏል።
ሂደቱ የትምህርት ተደራሽነትን ከማረጋገጥ አንጻር ዋጋ ቢኖረውም በትምህርት ጥራትና ምርምር ዘርፉ ላይ ብዙ ጥያቄ ሲነሳበት ቆይቷል።
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴርም ምክር ቤቱን ለማቋቋም የፈለገው በእነዚሁ ምክንያቶች መሆኑን አስታውቋል።
የልማት ዘርፉ የሳይንስ ምርምርን እንደመጠየቁ በተለይ በቴክኖሎጂ ፣ በጤና፣ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ዘርፍ የ3ኛ ድግሪን ተደራሽነት ማረጋገጥ ላይ ትኩረት ሰጥቷል።
ምክር ቤቱ እነዚህን ጨምሮ የሚኒስቴሩን እቅድ ከግብ ለማድረስ እንደሚያግዝ ይጠበቃል።
የምክር ቤቱ አባልና የመድረኩ ተሳታፊ ፕሮፌሰሮችም ከፋና ቴሌቪዥን ጋር በነበራቸው ቆይታ መንግስት ከምሁራን ጋር ለመስራት የጀመራቸው እንቅስቃሴዎች ተስፋ ሰጪ በመሆናቸው እነሱም በተሰጣቸው ሀላፊነት ለመስራት መምጣታቸውን ገልጸዋል።
በፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ሰብሳቢነት የሚመራው ካውንስሉ በቀጣይ በዝርዝር የሚሰራቸውን ተግባሮች ተፈጻሚ ለማድረግ አወቃቀር የዘረጋ ሲሆን ለክትትሉ ቋሚ ቋሚቴዎችን አዋቅሯል።
በሀይለኢየሱስ ስዩም
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!