የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ነብያት ጌታቸው በአልጄሪያ የቻይና አምባሳደር ሊ ሊያንሄ ጋር ተወያዩ

By Abrham Fekede

January 25, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአልጀርያ የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ነብያት ጌታቸው በአልጄሪያ የቻይና አምባሳደር ከሆኑት ሊ ሊያንሄ ጋር ተወያዩ፡፡

ውይይቱ በቻይና አፍሪካ ትብብርና በሌሎች የሁለትዮሽ ትብብር ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ ነው ተብሏል።

አምባሳደሩ በመንግስት በኩል በትግራይ ክልል አስፈላጊ የሆኑ የሰብዓዊ ድጋፍ እና የህክምና ቁሳቁሶችን ለተጎጅዎች ለማድረስ እየተደረገ ስላለው ከፍተኛ ጥረት ገለጻ አድርገውላቸዋል።

በተጨማሪም በሌሎች ቀጠናዊና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ገለጻ ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!