የሀገር ውስጥ ዜና

ከሳዑዲ አረቢያ በሳምንቱ 1 ሺህ ኢትዮጵያውያንን የመመለስ ስራ ተጀመረ

By Tibebu Kebede

January 26, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ከሳዑዲ አረቢያ በሳምንቱ 1 ሳምንቱ ኢትዮጵያውያንን የመመለስ ስራ መጀመሩን በሀገሪቱ ያለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ።

ወደ ሳዑዲአረቢያ ህጋዊ ባልሆኑ መንገዶች ሲገቡ ተይዘው በሳዑዲ አረቢያ የተለያዩ የስደተኞች ማቆያ ጣብያ ውስጥ የሚገኙና ላለፉት ወራት ከኮሮና ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ ወደ ሀገር መመለስ ያልቻሉ የነበሩ ዜጎችን በስፋት ወደ ሀገር የመመለስ ስራ መጀመሩ  ኤምባሲው አስታውሷለል።

በዚሁ መሰረት በጅዳ ሹሜሲ የህገወጥ ስደተኞች ማቆያ ውስጥ የነበሩ የመጀመርያዎቹ 296 ኢትዮጵያውያን ወንድ ስደተኞች በዛሬው ዕለት ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ቅድመ ዝግጅቶች ተጠናቀዋል ተብሏል።

ይህ ዜጎችን የመመለስ ስራ መንግስት ከሳዑዲ አረቢያ ወገን ጋር ባደረገው ስምምነትና በተቀመጡ አቅጣጫዎች መሰረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተጠቁሟል።

በዚህም በየሳምንቱ 1 ሺህ ተመላሾች ወደ ሀገር የሚገቡ ሲሆን ወደፊት በመንግስት በኩል በሚሰጡ አቅጣጫዎች መሰረት የተመላሾች ቁጥር ይጨምራል ተብሎ እንደሚጠበቅ መረጃው አመልክቷል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!