አዲስ አበባ ፣ ጥር 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በትግራይ ክልል እየተደረገ ስለሚገኘው የሰብዓዊ ድጋፍ በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስተባባሪ ከሆኑትን ዶ/ር ካትሪን ሶዚን ጋር ተወያዩ።
ሚኒስትሯ በክልሉ የመንገድ፣ የባንክ፣ እንዲሁም የቴሌኮም አገልግሎት ወደ ነባራዊ ሁኔታው እየተመለሰ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
መንግስት በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል የህግ ማስከበር ሂደቱን ተከትሎ ጫና የደረሰባቸው ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም ከፍታኛ ትኩረት ሰጥቶ አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
ስለሁኔታው የተዛባ መረጃ እየተሰራጨ መሆኑ እንዳሳሰባቸው አንስተዋል።
ዶ/ር ካትሪን ሶዚ በበኩላቸው፣ ክስተቱን ተከትሎ መንግስት እያደረገ ያለው ፈጣን ምላሽ የሚደነቅ እንደሆነ ተናግረው፣ ከሁኔታው ጋር ተያይዞ የተሰራጩትን የተዛቡ መረጃዎችን በድርጅታቸው በኩል ለማጣራት እንደሚንቀሳቀሱ ተናግረዋል።
ሁለቱ አካላት በቀጣይነት በሰሜኑ የሃገሪቱ ክፍል ለሚደረጉ ሰብዓዊ ድጋፎች ትስስራቸውን አጠናክረው በጋራ እንደሚሰሩ መግለጻቸውን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!